Released on May 2, 2017

Thumbnail

ሠምበሬ

ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ

ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ

አምና ፍቅር ጎድቶኝ ከአካል ከልቤ ላይ ሳይጠፋ ሰምበሬ

ደግሞ ሌላ አገኘኝ አዲስ ገላ ለብሶ እዩትና ዛሬ

ሰው መውደድ ዕርሜ ነው

እያልኩኝ ፎክሬ

ያንን ጉራ ሁላ

ገላ ናድው ዛሬ

ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ

ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ

አምና ፍቅር ጎድቶኝ ከአካል ከልቤ ላይ ሳይጠፋ ሰምበሬ

ደግሞ ሌላ አገኘኝ አዲስ ገላ ለብሶ እዩትና ዛሬ

አልደክምም ቃሌ ነው

እያልኩኝ ፎክሬ

ያንን ጉራ ሁላ

ቀን አራደው ዛሬ

ያን ጉራ ሁላ ጉራ ሁላ

ያን ጉራ ሁላ ትታ ነፍሴ

ወኔዬ ከዳኝ ወንድነቴ

ወድቆ ጨነቀኝ ኩራቴ

የቅብጥ ሐሳብ ጤዛ ነው ሲነጋ ረጋፊ

ወትሮም በአፍ ቃል ይፈጥናል ቀድሞ ተሸናፊ

ላያድን ቃል ብቻ

ምን ያደርጋል ዛቻ

ጉራ ብቻ

አዝማች

ያን ጉራ ሁላ ጉራ ሁላ

ያን ጉራ ሁላ ትታ ነፍሴ

ወኔዮ ከዳኝ ወንድነቴ

ወድቆ ጨነቀኝ ኩራቴ

ስማ

ስማ

ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ… ጉራ ብቻ

ቦታ ቢለዋወጥ ወጥ ላያጥም ጉልቻ… ጉራ ብቻ

ልቤ ዛሬም ወደህ ልትሆን መተረቻ… ጉራ ብቻ

ታዲያ ምን አመጣው ያንን ሁሉ ዛቻ … ጉራ ነው ከአካሌ

ከአካሌ ሳይጠፋ ስምበሬ

ከአካሌ ሳይጠፋ ስምበሬ

ታላቅና ታናሽ ምላስ እና ሰምበር … ጉራ ብቻ

ያስገምታል ስጋ ሞቶ ለሚቀበር … ጉራ ብቻ

ወርቅ የዘጋ ሳጥን ቁልፍ የሌለው መፍቻ … ጉራ ብቻ

ምን ያደርጋል ወድቀው አለሁ ማለት ብቻ … ጉራ ነው ከአካሌ

ከአካሌ ሳይጠፋ ስምበሬ

ከአካሌ ሳይጠፋ ስምበሬ