የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል
ተሸፈና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል
የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ
ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ
ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ
ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ
(ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ
ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ)
ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም
እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም
(ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም
እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም)
ፍቅር የበዛባት ዘልቆ ከማንኩሳ
መንናለች ቢሉኝ ቢጫ ልብስ ለብሳ
ሸዋ ከሩፋኤል ስጠብቃት ኖሬ
ንቤ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ
ሲኖዳ ዮሐንስ ያመት ወዜን ይዤ
ጋማ ሽጦ ካሳ ሸኝቶኝ ከወንዜ
መጥቼ ከሸዋ ስጠብቃት ኖሬ
ለካ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ
መጥቼ ከሸዋ ስጠብቃት ኖሬ
ለካ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ
ሀ ብለህ ተው ድገም ሲሉኝ ንስሀ አባቴ
ዋ ብየ ተማርኩኝ አይ አለመስማቴ
ቀለም ወርቄ ቢሆን የቅርቤ ጓደኛ
ፍቅር ለያዘው ሰው ከልካይ የለው ዳኛ
አሁን በማ ትኬ ይህ ልቤን ልካሰው
አንዴ በሷ ፍቅር የተረታሁኝ ሰው
የት እርቄስ ላገኝ ከፍቅሯ መሸሻ
እሷ ሆኖ ለኔ የአለም መጨረሻ
ማር ጧፍ ሁኔማር ጧፍ ሁና
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ
ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ
ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ
ያቺ ወንጌል ቢጫ ለብሳ
ከ'ንግዲህማ ቆብ አስጥዬ
እንዳልወስዳት አባብዬ
ሰብልዬ ናት እማሆዬ
ሰብልዬ ናት እማሆዬ
ሰብል አለም በቢጫው ቀለም
ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም
ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
ኦሆ…
የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል
ተሸፍና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል
የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ
ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ
ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ
ተረሳሽ ወይ የ'ሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ
(ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ
ተረሳሽ ወይ የ'ሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ)
ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም
እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም
(ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም
እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም)
ላሳደገኝ ደብር የሥለት ልጅ ሆኜ
ካሕን እንዴት ይፍታኝ ያንቺ እስረኛ ሆኜ
በጊዜ ተደፋ የቀለሙ ቀንዴ
የኔ ፊደል ማወቅ ካንቺ አዳነኝ እንዴ
ሳዋህድ ከኖርኩት ቅኔን ከደብተሬ
ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ
ለካ ሰው አይድንም በደገመው መጽሐፍ
እንደሰም አቅልጦ ፍቅር ካረገው ጧፍ
ለካ ሰው አይድንም በኦሪቱ ገድል
ወንጌል ይዞ መጥቶ ፍቅር ካረገ ድል
ማር ሲገባ ገዳም ድንጋይ ተንተርሶ
ጧፉም እንደ መናኝ እዩት ቢጫ ለብሶ
ወንጌል መነኮሱ በልጅነታቸው
ማር እስከጧፍ ሆኖ አለም ቢነዳቸው
አንቺ የፍቅር ጥጌ ውድነሽ በጣሙን
መምጣቴ ነው በቃ እኔ አቃተኝ አሁን
አዲስ አለም ሆነ ባንቺ ስለ ወጋየሁ
እድሌ ሆነና ባጣሽ ተሰቃየው
ማር ጧፍ ሁኔ ማር ጧፍ ሁና
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማሬ ማሬ ጎጃም ኑራ ማሬ
ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ
ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ
ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ
ያቺ ወንጌል ቢጫ ለብሳ
ከ'ንግዲህማ ቆብ አስጥዬ
እንዳልወስዳት አባብዬ
ሰብልዬ ናት እማሆዬ
ሰብልዬ ናት እማሆዬ
ሰብል አለም በቢጫው ቀለም
ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም
ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
ኦሆ…
ዘንግ ይዛ ማር ዘንግ ይዛ…